አሞጽ 5:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮንን የሠራ፣ ጨለማውን ወደ ንጋት ብርሃን የሚለውጥ፣ ቀኑን አጨልሞ ሌሊት የሚያደርግ፣ የባሕሩንም ውሃ ጠርቶ፣ በገጸ ምድር ላይ የሚያፈስስ፣ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረውን፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጠውን፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልመውን፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸውን፥ |
ዕውሮችን በማያወቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ። ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ። ይህን አደርጋለሁ፤ አልተዋቸውም።
በቅጥሩ ላይ እንደ ዕውር ተደናበርን፤ አካሄዳችንም ዐይን እንደሌላቸው በዳበሳ ሆነ፤ ጀንበር በምትጠልቅበት ጊዜ እንደሚሆነው በእኩለ ቀን ተደናበርን፤ በብርቱዎች መካከልም እንደ ሙታን ሆንን።
ተራሮችን የሚሠራ፣ ነፋስን የሚፈጥር፣ ሐሳቡንም ለሰው የሚገልጥ፣ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፣ የምድርንም ከፍታዎች የሚረግጥ፣ ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
መኖሪያውን በሰማይ የሚሠራ፣ መሠረቱንም በምድር የሚያደርግ፣ የባሕርን ውሃ የሚጠራ፣ በምድርም ገጽ ላይ የሚያፈስስ፣ እርሱ ስሙ እግዚአብሔር ነው።