አሞጽ 3:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወጥመድ ሳይዘረጋ፣ ወፍ በምድር ላይ ይጠመዳልን? የሚይዘው ነገር ሳይኖርስ፣ ወጥመዱ ከምድር ይፈነጠራልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ወፍ፥ የሚያጠምደው ነገር ሳይኖር፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ነገር ሳይዝ ከምድር ይፈነጠራልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወፍ ያለ ማጥመጃ ወጥመድ ውስጥ ገብቶ ይያዛልን? ወጥመድስ አንዳች ነገር ሳይነካው ይፈናጠራልን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር በከንቱ ይፈናጠራልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ወፍ፥ አጥማጅ ከሌለው፥ በምድር ላይ በወጥመድ ይያዛልን? ወይስ ወስፈንጠር አንዳች ሳይዝ ከምድር ይፈነጠራልን? |
ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።
ልነቅላቸውና ላፈርሳቸው፣ ልገለብጣቸውና ላጠፋቸው፣ መከራም ላመጣባቸው እንደ ተጋሁ ሁሉ፣ ላንጻቸውና ልተክላቸው ደግሞ እተጋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።