ሐዋርያት ሥራ 8:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተበተኑትም አማኞች በሄዱበት ስፍራ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተበተኑት ግን እየተዘዋወሩ የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ፥ አስተማሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተበተኑትም ቃሉን እየሰበኩ ዞሩ። |
በእስጢፋኖስ ላይ በተነሣው ስደት ምክንያት የተበተኑት አማኞች ቃሉን ለአይሁድ ብቻ እየተናገሩ እስከ ፊንቄ፣ እስከ ቆጵሮስና እስከ አንጾኪያ ድረስ ዘለቁ።
ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በነበረችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያትም በቀር አማኞች በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ፤
እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ መከራ ተቀብለን ተንገላታን፤ ነገር ግን ብርቱ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ፣ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንደምናበሥር በአምላካችን ድፍረት አገኘን።