ሐዋርያት ሥራ 7:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብም፣ በግብጽ የነበረው የሕዝባችን ቍጥር እየበዛ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብጽ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብጽ በዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር ለአብርሃም በመሐላ የሰጠው ተስፋ የሚፈጸምበት ጊዜ ሲቃረብ በግብጽ የነበረው የሕዝባችን ቊጥር እየበዛ ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን በደረሰ ጊዜ እስራኤል በዙ፤ የግብፅንም ሀገር መሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአብርሃም የማለለት የተስፋው ዘመን ሲቀርብ፥ ዮሴፍን የማያውቀው ሌላ ንጉሥ በግብፅ ላይ እስኪነሣ ድረስ፥ ሕዝቡ እየተጨመሩ በግብፅ በዙ። |