ሐዋርያት ሥራ 4:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም አለቆቻቸውና፣ ሽማግሌዎቻቸው እንዲሁም ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ የአይሁድ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ የሕግ መምህራንም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማግሥቱም አለቆቻቸውና ሽማግሎች፥ ጻፎችም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ |
ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።
ወዲያውም በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሐፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋራ ከተማከሩ በኋላ፣ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።
አንድ ቀን ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምርና ወንጌልን ሲሰብክ የካህናት አለቆች፣ ጸሐፍትና ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ።
ነገር ግን በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ የተከበረ አንድ የሕግ መምህር፣ እርሱም ገማልያል የሚሉት ፈሪሳዊ ተነሥቶ በሸንጎው መካከል ቆመና ሐዋርያትን ወደ ውጭ አውጥተው ለጥቂት ጊዜ እንዲያዩአቸው አዘዘ፤