ሐዋርያት ሥራ 4:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጠሯቸውም በኋላ፣ በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዟቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ጠሩአቸውና የኢየሱስን ስም በመጥራት ከቶ እንዳይናገሩ ወይም እንዳያስተምሩ በጥብቅ አዘዙአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠርተውም፦“ በኢየሱስ ስም ፈጽሞ አትናገሩ አታስተምሩም” ብለው አዘዙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። |
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
“በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞላችኋት፤ ደግሞም እኛን ለዚህ ሰው ደም ተጠያቂዎች ልታደርጉን ቈርጣችሁ ተነሣችሁ።”