ሐዋርያት ሥራ 27:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ሰዎች፤ ጕዞው አደገኛ እንደሚሆን፣ በመርከቡና በጭነቱ እንዲሁም በእኛ በራሳችን ላይ እንኳ ትልቅ ጕዳት እንደሚደርስ ይታየኛል” ብሎ አስጠነቀቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህ ጉዞ በጥፋትና በብዙ ጉዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም፤” ብሎ መከራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ ሰዎች! ከእንግዲህ ወዲህ ያለው ጒዞአችን አደጋ እንዳለበት ይታየኛል፤ በጭነቱና በመርከቡ ላይ ብቻ ሳይሆን በሰው ሕይወትም ላይ ብርቱ ጒዳትና ጥፋት ይደርሳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ስሙኝ፤ ጕዞአችን በብዙ ጭንቀትና በከባድ ጥፋት ላይ ሆኖ አያለሁ፤ ይህንም የምለው ጥፋቱ በራሳችንም ሕይወት እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ ስላልሆነ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ይህ ጕዞ በጥፋትና በብዙ ጕዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም” ብሎ መከራቸው። |
ይህ ምስጢር ለእኔ የተገለጠው፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ ታላቅ ጥበብ ስላለኝ አይደለም፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትርጕሙን እንድታውቅና በአእምሮህ ታሰላስለው የነበረው ነገር ምን እንደ ሆነ ትረዳ ዘንድ ነው።
ቆጵሮስ በታየችን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት ዐለፍንና ወደ ሶርያ አመራን፤ መርከባችን ጭነቱን በጢሮስ ማራገፍ ስለ ነበረበት እኛም እዚያው ወረድን።