ሐዋርያት ሥራ 26:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ፣ እግዚአብሔር ሙታንን ማስነሣት እንደማይችል አድርጋችሁ የምትቈጥሩት ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ እንደሆነ ስለምን በእናንተ ዘንድ የማይታመን ነገር ሆኖ ይቆጠራል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ መሆኑ ስለምን በእናንተ ዘንድ ሊታመን የማይቻል ሆነ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴትስ እግዚአብሔር ሙታንን እንደሚያስነሣቸው በእናንተ ዘንድ የማይታመን ሆኖ ይቈጠራል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ሙታንን የሚያስነሣ እንደ ሆነ ስለ ምን በእናንተ ዘንድ የማይታመን ነገር ሆኖ ይቈጠራል? |
ጳውሎስም ሕዝቡ፣ ከፊሎቹ ሰዱቃውያን፣ ከፊሎቹ ፈሪሳውያን መሆናቸውን ስላወቀ፣ “ወንድሞቼ ሆይ፤ እኔ ከፈሪሳዊ የተወለድሁ ፈሪሳዊ ነኝ፣ ለፍርድ የቀረብሁትም የሙታንን ትንሣኤ ተስፋ በማድረጌ ነው” ሲል በሸንጎው ፊት ጮኸ።