ሐዋርያት ሥራ 2:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ እያንዳንዳችን በተወለድንበት፣ በራሳችን ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው እንዴት ቢሆን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋ ችንን እንዴት እንሰማለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኛ በየትውልድ አገራችን ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው እንዴት ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በየሀገራችን ቋንቋ ሲናገሩ እንዴት እንሰማቸዋለን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም እያንዳንዳችን የተወለድንበትን የገዛ ቋንቋ ችንን እንዴት እንሰማለን? |
እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቧል።