ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ሄደን፣ እያንዳንዳችን ምሰሶ ቈርጠን እናምጣ፣ በዚያም የምንቀመጥበትን መኖሪያ እንሥራ።” እርሱም፣ “ይሁን ሂዱ” አላቸው።
ሐዋርያት ሥራ 18:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም እንደ እነርሱ ድንኳን ሰፊ ስለ ነበረ፣ ከእነርሱ ጋራ ተቀምጦ በተመሳሳይ ሥራ ላይ ተሰማራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ሥራ ልክ እንደ እነርሱ ድንኳን መስፋት ስለ ነበር ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ አብሮአቸው ይሠራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራቸው አንድ ስለ ነበረ ድንኳን ሰፊዎችም ስለ ነበሩ ከእነርሱ ጋር አብሮ ኖረ፤ በአንድነትም ይሠሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና። |
ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ሄደን፣ እያንዳንዳችን ምሰሶ ቈርጠን እናምጣ፣ በዚያም የምንቀመጥበትን መኖሪያ እንሥራ።” እርሱም፣ “ይሁን ሂዱ” አላቸው።
እኔ ግን ከእነዚህ መብቶች በአንዱ እንኳ አልተጠቀምሁም፤ አሁንም ይህን የምጽፍላችሁ እንደነዚህ ያሉትን ነገሮች ታደርጉልኛላችሁ በሚል ተስፋ አይደለም፤ ማንም ትምክሕቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛልና።
ከእናንተም ጋራ ሳለሁ አንዳች ባስፈለገኝ ጊዜ፣ ከመቄዶንያ የመጡ ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ስለ ሰጡኝ ለማንም ሸክም አልሆንሁም። በእናንተ ላይ በምንም ነገር ሸክም እንዳልሆን ተጠንቅቄአለሁ፤ ወደ ፊትም እጠነቀቃለሁ።
ወንድሞች ሆይ፤ ጥረታችንንና ድካማችንን ታስታውሳላችሁ፤ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እየሠራን የእግዚአብሔርን ወንጌል ሰበክንላችሁ።