ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
2 ተሰሎንቄ 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱም ያበረታችኋል፤ ከክፉውም ይጠብቃችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌታ የታመነ ነው፤ እርሱም ያጸናችኋል ከክፉውም ይጠብቃችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ግን ታማኝ ነው፤ እርሱ ያበረታችኋል፤ ከሰይጣንም ይጠብቃችኋል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው። |
ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
ያቤጽም፣ “አቤቱ፤ እንድትባርከኝ፣ ግዛቴንም እንድታሰፋልኝ እለምንሃለሁ፤ እጅህ ከእኔ ጋራ ትሁን፤ ከሥቃይና ከጕዳትም ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ጮኸ። እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ስለዚህ ስትነጋገሩ ቃላችሁ፣ ‘አዎን’ ከሆነ ‘አዎን’፤ ‘አይደለም’ ከሆነ ‘አይደለም’ ይሁን፤ ከዚህ ውጭ የሆነ ሁሉ ከክፉው የሚመጣ ነውና።
በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።
ጌታ፣ በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።