2 ነገሥት 21:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምናሴ ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ተግባር፣ የሠራውን ኀጢአት ጨምሮ የፈጸመው ድርጊት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናሴ ያደረገው ሌላው ነገርና የፈጸመው ኃጢአት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናሴ ያደረገው ሌላው ነገርና የፈጸመው ኃጢአት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናሴም የቀረው ነገርና የሠራው ሥራ ሁሉ፥ ያደረገውም ኀጢአት፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናሴም የቀረው ነገርና የሠራው ሥራ ሁሉ፥ ያደረገውም ኀጢአት፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? |