ከዚህ የተነሣ ፍልስጥኤማውያን፣ አባቱ አብርሃም በሕይወት በነበረበት ጊዜ፣ የአብርሃም አገልጋዮች የቈፈሯቸውን የውሃ ጕድጓዶች በሙሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኗቸው።
2 ነገሥት 19:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባዕድ ምድር የውሃ ጕድጓዶችን ቈፈርሁ፤ በዚያም ውሃ ጠጣሁ። የግብጽን ምንጮች ሁሉ፣ በእግሬ ረግጬ አደረቅሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘በባዕድ አገር ጉድጓድ ቆፍሬ፥ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ’ ብለህ ታብየሃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በባዕድ አገር ጒድጓድ ቆፍሬ፥ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ’ ብለህ ታብየሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕረፍት አደረግሁ፤ የባዕድ ውኃንም ጠጣሁ፥ የተገደበውንም ውኃ ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቈፈርሁም፤ እንግዳውንም ውሃ ጠጣሁ፤ የተገደበውንም ውሃ ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ፤” ብለህ በመልእክተኞችህ እጅ በእግዚአብሔር ላይ ተገዳደርህ። |
ከዚህ የተነሣ ፍልስጥኤማውያን፣ አባቱ አብርሃም በሕይወት በነበረበት ጊዜ፣ የአብርሃም አገልጋዮች የቈፈሯቸውን የውሃ ጕድጓዶች በሙሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኗቸው።
ከዚያም ቤን ሃዳድ፣ “ለሚከተለኝ ሰው ሁሉ የሰማርያ ዐፈር አንዳንድ ዕፍኝ የሚዳረስ ሳይሆን ቢቀር፣ አማልክት ይህን ያድርጉብኝ፤ ከዚህ የባሰም ያምጡብኝ” ሲል ሌሎች መልክተኞችን ወደ አክዓብ ላከ።
ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፤ እማርካቸዋለሁ፤ ምርኮን እካፈላለሁ፤ ነፍሴ በእነርሱ ትጠግባለች፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ትደመስሳቸዋለች አለ።’