La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 8:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም የጀመራችሁትን ተግባር በዐቅማችሁ መጠን ከፍጻሜ አድርሱት፤ ይህም ለመስጠት የነበራችሁ በጎ ፈቃድ እውን እንዲሆን ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም እንዳዐቅማችሁ መጠን ለማድረግ ያላችሁ ጉጉት እንደ ሐሳባችሁ እንዲሆንላችሁ የጀመራችሁትን ከፍጻሜ አድርሱት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ የመስጠት ፈቃደኛነታችሁ አሳብ በሥራ ላይ ውሎ ወደ ፍጻሜ እንዲደርስ ባላችሁ መጠን ያንን ያሰባችሁትን አሁን አድርጉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁ​ንም አድ​ርጉ፤ ፈጽ​ሙም፤ መፍ​ቀድ ከመ​ሻት ነውና፤ ማድ​ረ​ግም ከማ​ግ​ኘት ነውና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁንም ለማሰብ በጎ ፈቃድ እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እንዳላችሁ መጠን መፈጸም ደግሞ ይሆን ዘንድ፥ ማድረጉን ደግሞ ፈጽሙ።

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 8:11
5 Referencias Cruzadas  

“ስጦታ እንዲያመጡልኝ ለእስራኤላውያን ንገራቸው። ይሰጥ ዘንድ ልቡ ካነሣሣው ከእያንዳንዱ ሰው ስጦታን ተቀበልልኝ።


ለመስጠት በጎ ፈቃድ ካለን ስጦታው ተቀባይነት የሚያገኘው ባለን መጠን ስንሰጥ እንጂ፣ በሌለን መጠን ለመስጠት ስንሞክር አይደለም።


ከዚህም በላይ ስጦታውን በምንወስድበት ጊዜ ዐብሮን እንዲሄድ በአብያተ ክርስቲያናት ተመርጧል፤ ስጦታውንም የምንወስደው ጌታን ራሱን ለማክበርና ሌሎችን ለመርዳት ካለን በጎ ፈቃድ የተነሣ ነው።


እንደ ዐቅማቸው ብቻ ሳይሆን፣ ከዐቅማቸው በላይ በፈቃዳቸው እንደ ሰጡ እመሰክርላቸዋለሁ።


ምክንያቱም ሌሎችን ለመርዳት ያላችሁን በጎ ፈቃድ ዐውቃለሁ፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እናንተ በአካይያ የምትኖሩ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ እንደ ሆናችሁ ለመቄዶንያ ሰዎች አፌን ሞልቼ ተናግሬአለሁ፤ ቅን ፍላጎታችሁም ብዙዎችን ለበጎ ሥራ አነሣሥቷል።