ተለይቼህ ስሄድ የእግዚአብሔር መንፈስ የት እንደሚወስድህ አላውቅም፤ ታዲያ ሄጄ ለአክዓብ ከነገርሁት በኋላ ሳያገኝህ ቢቀር እኔን ይገድለኛል፤ ነገር ግን እኔ ባሪያህ ከጕልማሳነቴ ጀምሮ እግዚአብሔርን አመልካለሁ።
2 ቆሮንቶስ 12:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ የተነጠቀ በክርስቶስ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ የተነጠቀው በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት፥ በሥጋ ይሁን ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም እግዚአብሔር ይወቀው፥ እስከ ሦስተኛ ሰማይ ድረስ የተነጠቀ በክርስቶስ አንድ ሰው አውቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ተወሰደ፤ (የተወሰደውም ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል።) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክርስቶስ ያመነ አንድ ሰው አውቃለሁ፤ ዘመኑ ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት ነው፤ ነገር ግን በሥጋው ይሁን በነፍሱ እንጃ፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ ያን ሰው እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ነጥቀው ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን በክርስቶስ አውቃለሁ፥ በሥጋ እንደ ሆነ አላውቅም ወይም ከሥጋ ውጭ እንደ ሆነ አላውቅም፥ እግዚአብሔር ያውቃል፤ እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ። |
ተለይቼህ ስሄድ የእግዚአብሔር መንፈስ የት እንደሚወስድህ አላውቅም፤ ታዲያ ሄጄ ለአክዓብ ከነገርሁት በኋላ ሳያገኝህ ቢቀር እኔን ይገድለኛል፤ ነገር ግን እኔ ባሪያህ ከጕልማሳነቴ ጀምሮ እግዚአብሔርን አመልካለሁ።
“ነገር ግን አምላክ በርግጥ በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፤ ሰማይ፣ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ እንኳ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ታዲያ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ!
ከዚያም፣ “እነሆ፤ እኛ አገልጋዮችህ እዚህ ዐምሳ ጠንካራ ሰዎች አሉን፤ ምናልባትም የእግዚአብሔር መንፈስ ጌታህን አንሥቶ ከአንዱ ተራራ ላይ አስቀምጦት ወይም ከአንዱ ሸለቆ አግብቶት ይሆናልና እስኪ ሄደው ይፈልጉት” አሉት። ኤልሳዕም፣ “አይሆንም፤ አትላኳቸው” አለ።
ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።
መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ በተሰጠው ራእይም በባቢሎን ምድር ወደ ነበሩት ምርኮኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ወጥቶ ሄደ፤
ከእኔ ጋራ ታስረው ለነበሩት ዘመዶቼ ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሰላምታ አቅርቡልኝ፤ እነርሱ በሐዋርያት መካከል ስመጥሮችና በክርስቶስ በማመንም እኔን የቀደሙ ናቸው።
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?
ከዚያም በኋላ እኛ የቀረነው፣ በሕይወትም የምንኖረው ጌታን በአየር ላይ ለመቀበል ከእነርሱ ጋራ በደመና እንነጠቃለን፤ በዚህም መሠረት ለዘላለም ከጌታ ጋራ እንሆናለን።
ክርስቶስ የእውነተኛዪቱ ድንኳን ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደ ተሠራችው መቅደስ አልገባም፤ ነገር ግን አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ እርሷ፣ ወደ ሰማይ ገባ።