2 ቆሮንቶስ 11:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክርስቶስ እውነት በውስጤ እስካለ ድረስ፣ በአካይያ አውራጃ ይህን ትምክሕቴን ማንም ሊገታው አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ፥ ይህ ትምክህቴ በአካይያም አገር ዝም የሚያሰኘኝ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ በመኖሩ እንዳልመካ የሚያደርገኝ በአካይያ አገሮች ማንም የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስ ዕውነት አብሮኝ ይኖራልና፥ ይህቺ ደስታዬ በአካይያ አውራጃ አልተከለከለችብኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክርስቶስ እውነት በእኔ እንዳለ፥ ይህ ትምክህት በእኔ ዘንድ በአካይያ አገር አይከለከልም። |
አጵሎስ ወደ አካይያ ለመሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ወንድሞች አበረታቱት፤ በዚያ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም እንዲቀበሉት ደብዳቤ ጻፉለት። እዚያም በደረሰ ጊዜ ከጸጋው የተነሣ አምነው ለነበሩት ትልቅ ረዳት ሆናቸው፤
በእነርሱ ቤት ላለች ቤተ ክርስቲያንም ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእስያ አገር ለመጀመሪያ ወደ ክርስቶስ ለተመለሰው፣ ለወዳጄ ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እለምናችኋለሁ፤
በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤
ደግሞም ሌሎች በደከሙበት ሥራ ከመጠን በላይ በመመካት ከተመደበልን ወሰን አናልፍም፤ ይልቁንም እምነታችሁ እያደገ በሄደ ቍጥር በእናንተ ዘንድ የተመደበልን አገልግሎት እየሰፋ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን።
እስከ አሁን ድረስ በእናንተ ፊት ራሳችንን ስንከላከል የኖርን ይመስላችኋልን? በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት እንናገራለን፤ ደግሞም ወዳጆች ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምናደርገው እናንተን ለማነጽ ነው።
ምክንያቱም ሌሎችን ለመርዳት ያላችሁን በጎ ፈቃድ ዐውቃለሁ፤ ካለፈው ዓመት ጀምሮ እናንተ በአካይያ የምትኖሩ ሌሎችን ለመርዳት ዝግጁ እንደ ሆናችሁ ለመቄዶንያ ሰዎች አፌን ሞልቼ ተናግሬአለሁ፤ ቅን ፍላጎታችሁም ብዙዎችን ለበጎ ሥራ አነሣሥቷል።
ከእንግዲህ እኔ አልኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በውስጤ ይኖራል። አሁንም በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለኝ እምነት ነው።
በእናንተ በምታምኑት መካከል ሳለን እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅ እንዲሁም ያለ ነቀፋ ሆነን እንደ ኖርን እናንተም እግዚአብሔርም ምስክሮች ናችሁ።
የሽንገላ ቃል ከቶ እንዳልተናገርን ወይም ሥሥትን ለመሸፈን ብለን አስመሳዮች እንዳልሆንን ታውቃላችሁ፤ ለዚህም እግዚአብሔር ምስክራችን ነው።
እኔም ለዚህ ነገር የምሥራች አብሣሪና ሐዋርያ እንዲሁም ለአሕዛብ የእውነተኛ እምነት አስተማሪ ሆኜ ተሾምሁ፤ እውነቱን እናገራለሁ፤ አልዋሽም።