በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሥርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ።
2 ቆሮንቶስ 1:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን ነገር አንጽፍላችሁም፤ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልታነብቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን የተለየ ነገር አንጽፍላችሁም፥ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንብባችሁ ማስተዋል የምትችሉትን ነገር ካልሆነ ሌላ ምንም አንጽፍላችሁም፤ በሙሉ ማስተዋል እንደምትችሉ ተስፋ አደርጋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምታነቡትንና የምታውቁትን ነው እንጂ፥ ሌላ የምንጽፍላችሁ የለምና፥ ይህንም እስከ ፍጻሜ እንደምታስተውሉት ተስፋ አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምታነቡትና ከምታስተውሉት በቀር ሌላ አንጽፍላችሁምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ ደግሞ ትምክህታችን እንደምትሆኑ እንዲሁ ትምክህታችሁ እንድንሆን፥ በከፊል ስለ እኛ እንዳስተዋላችሁ ፈጽማችሁ ታስተውሉት ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ። |
በነጋም ጊዜ፣ ወደ የብስ መቅረባቸውን አላወቁም ነበር፤ ነገር ግን ዳር ዳሩ አሸዋማ የሆነ የባሕር ሥርጥ አይተው፣ ቢቻላቸው መርከቡን ገፍተው ወደዚያ ለማድረስ ወሰኑ።
ነገር ግን ስውርና አሳፋሪ ነገሮችን ትተናል፤ በማታለል አንመላለስም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ከሐሰት ጋራ አንቀላቅልም፤ ይልቁንም እውነትን በግልጽ እየተናገርን በሰው ሁሉ ኅሊና ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረን ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።
እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደ ሆነ ስለምናውቅ፣ ሰዎች የምንናገረውን እንዲቀበሉ ለማድረግ እንጥራለን። የእኛ ማንነት በእግዚአብሔር ዘንድ የተገለጠ ነው፤ ደግሞም በኅሊናችሁ ዘንድ ግልጽ ነው ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።