ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት።
1 ጢሞቴዎስ 5:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማኝ የሆነች ማንኛዋም ሴት በቤተ ሰቧ ውስጥ መበለቶች ቢኖሯት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መበለቶችን ብቻ መርዳት እንድትችል እርሷው ትርዳቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዲሆኑ አትተዋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማኝ የሆነች ማንም ሴት መበለታት ዘመዶች ቢኖሩአት፥ እነርሱን ትርዳቸው፤ ቤተክርስትያንም በእርግጥ እርዳታ የሚያሻቸውን መበለታትን መርዳት እንድትችል ሸክም አይሁኑባት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዲት አማኝ የሆነች ሴት በቤትዋ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ቢኖሩአት የቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዳይሆኑ እርስዋ ትርዳቸው፤ በዚህ ዐይነት ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ ረዳት የሌላቸውን ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች መርዳት ትችላለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን ብትሆን፥ ይርዱአቸው፤ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልቴቶች ያሉት የሚያምን ቢሆን ወይም የምታምን ብትሆን፥ ይርዱአቸው፥ ቤተ ክርስቲያንም እውነተኞችን ባልቴቶች እንድትረዳ አይክበዱባት። |
ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት።