1 ጢሞቴዎስ 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ እግዚአብሔር አለና፤ ደግሞም በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል አንድ መካከለኛ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል አንድ አስታራቂ ደግሞ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አንድ ነው፤ በመካከል ሆኖ እግዚአብሔርንና ሰውን የሚያስታርቀውም አንድ ነው፤ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ |
“የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።
እንግዲህ፣ ለጣዖት የተሠዋ ሥጋ ስለ መብላት፣ በዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
ለእኛ ግን ሁሉም ነገር ከርሱ የሆነ፣ እኛም ለርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር በርሱ አማካይነት የሆነ፣ እኛም በርሱ አማካይነት የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።
ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው።
ስለዚህም የተጠሩት፣ ተስፋ የተሰጠውን የዘላለም ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፤ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር በነበሩበት ጊዜ ከሠሩት ኀጢአት ነጻ ለማውጣት ቤዛ ሆኖ ሞቷልና።
ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
በመቅረዞቹም መካከል “የሰው ልጅ የሚመስል” አየሁ፤ እርሱም እስከ እግሩ የሚደርስ መጐናጸፊያ የለበሰ፣ ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።