ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”
1 ጢሞቴዎስ 2:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴት በጸጥታና በሙሉ መገዛት ትማር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴት በሁሉ ነገር እየታዘዘች በጽሞና ትማር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴት በጸጥታና በመታዘዝ ትማር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤ |
ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”
የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።