ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፏል።
ምክንያቱም “እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ፤” ተብሎ ተጽፎአልና፤
“እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ” ተብሎ ተጽፎአል።
በዚያ አውራ ጐዳና ይሆናል፤ የተቀደሰ መንገድ ተብሎ ይጠራል። የረከሱ አይሄዱበትም፤ በመንገዱ ላይ ላሉት ብቻ ይሆናል፤ ቂሎችም አይሄዱም።
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ተለዩ፤ ቅዱሳንም ሁኑ፤ ምድር ለምድር በሚንቀሳቀስ በማንኛውም ፍጡር ራሳችሁን አታርክሱ።
አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ስለዚህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።
“ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ጉባኤ እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፤ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ።
“ ‘ራሳችሁን ቀድሱ፤ ቅዱሳንም ሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና።
በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ፣ ዐብረው መጓዝ ይችላሉን?