በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
1 ነገሥት 5:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጢሮስ ንጉሥ ኪራም በዘመኑ ሁሉ ለዳዊት ወዳጅ ስለ ነበር፣ ሰሎሞን በአባቱ እግር ለመተካት መቀባቱን በሰማ ጊዜ፣ መልእክተኞቹን ወደ ሰሎሞን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቆይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ከዳዊት ጋር ወዳጅነቱን አጽንቶ ቈይቶ ነበር፤ ሰሎሞን በአባቱ በዳዊት እግር መንገሡን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ መልእክተኞቹን ላከ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለአባቱ ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገልጋዮቹን ወደ ሰሎሞን ላከ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ ባሪያዎቹን ወደ ሰሎሞን ሰደደ። |
በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ እንዲሁም የዝግባ ዕንጨት፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ድንጋይ ጠራቢዎችን ዐብሮ ሰደደ፤ እነርሱም ለዳዊት ቤተ መንግሥት ሠሩለት።
ቶዑ ከአድርአዛር ጋራ ሁልጊዜ ይዋጋ ስለ ነበር፣ ሰላምታና በአድርአዛር ላይ ስለ ተቀዳጀውም ድል የደስታ መግለጫ እንዲያቀርብለት፣ ልጁን ዮራምን ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው፤ እርሱም የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃ ይዞ መጣ።
በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤተ መንግሥት እንዲሠሩ መልክተኞችን፣ ድንጋይ ጠራቢዎችንና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችን ከዝግባ ዕንጨት ጋራ ላከ።
ከፍልስጥኤማውያንም አንዳንዶቹ ለኢዮሣፍጥ እጅ መንሻ አመጡለት፤ ጥሬ ብርም ገበሩለት፤ ዐረቦችም ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ በግና ሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አውራ ፍየል መንጋ አመጡለት።
ከዚህ በኋላ፣ ሰሎሞን ለጢሮስ ንጉሥ ለኪራም የሚከተለውን ይህን መልእክት ላከ፤ “አባቴ ዳዊት የሚኖርበትን ቤተ መንግሥት ሲሠራ እንደ ላክህለት ሁሉ፣ ለእኔም የዝግባ ዕንጨት ላክልኝ።
አሕዛብን ከፊትህ አስወጣለሁ፤ ድንበርህን አሰፋለሁ፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ማንም አይመኝም።
ስለ ጢሮስ የተነገረ ንግር፤ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፤ ዋይ በሉ! ጢሮስ ተደምስሳለችና፣ ያለ ቤትና ያለ ወደብ ቀርታለች። ከቆጵሮስ ምድር፣ ዜናው ወጥቶላቸዋል።
ቅርንጫፎቿ ለበትረ መንግሥት የሚሆኑ፣ ጠንካሮች ነበሩ፤ ጥቅጥቅ ባሉ ቅጠሎች መካከል፣ በቁመቷና በብዙ ቅርንጫፎቿ፣ ዘለግ ብላ፣ ጐልታ ትታይ ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
አንዳንድ ምናምንቴ ሰዎች ግን፣ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።