1 ነገሥት 4:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤ የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቆጣጣሪ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪያልም የቤት አዛዥ፥ ኤልያቅም የቤት አዛዦች አለቃ ነበረ፥ የሳፋን ልጅ ኤልያፍም የቤተ ሰብ ሐላፊ፥ የአዶን ልጅ አዶኒራምም ግብር አስገባሪ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሒሳርም የቤት አዛዥ፥ የዓብዳም ልጅ አዶኒራም አስገባሪ ነበረ። |
ንጉሥ ሮብዓም የጕልበት ሠራተኞች አለቃ የነበረውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን እስራኤል ሁሉ በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሡ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።
እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።
ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።
ንጉሥ ሮብዓም የጕልበት ሠራተኞች አለቃ የነበረውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን እስራኤላውያን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሡ ሮብዓም ግን እንደ ምንም ብሎ ሠረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ።
እስራኤላውያን ያላጠፏቸውን፣ በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው፤