1 ነገሥት 4:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃ ገዦች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡ የቅርብ አማካሪ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናታንም ልጅ ኦርኒያ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዘባት የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናታንም ልጅ ዓዛርያስ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዛቡድ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤ |
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።
እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።