1 ዮሐንስ 2:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ እርሱ የሰጠን ተስፋ የዘላለም ሕይወት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፥ እርሱም የዘለዓለም ሕይወት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ክርስቶስ የሰጠን ተስፋ የዘለዓለም ሕይወት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው። |
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በርሱ ላይ ዐትሟልና።”
ይህም የሆነው ኀጢአት በሞት እንደ ነገሠ ሁሉ፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ደግሞ የዘላለም ሕይወት ይገኝ ዘንድ ጸጋ በጽድቅ እንዲነግሥ ነው።
ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ በርሱ ለሚያምኑና የዘላለምን ሕይወት ለሚቀበሉ ወሰን የሌለው ትዕግሥቱን ከኀጢአተኞች ዋና በሆንሁት በእኔ እንደ ምሳሌ አድርጎ ያሳይ ዘንድ ምሕረትን አገኘሁ።
ይህም ሕይወት ተገለጠ፤ እኛም አይተናል፤ እንመሰክራለንም። ከአብ ዘንድ የነበረውን፣ ለእኛም የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት እንነግራችኋለን፤
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፣ እውነተኛ የሆነውን እርሱን እንድናውቅ ማስተዋልን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነተኛ በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አለን። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።