1 ዮሐንስ 2:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የወጡት ከእኛ መካከል ነው። ይሁን እንጂ ዱሮውንም ከእኛ ወገን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋርም ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን አለመሆናቸው እንዲታወቅ ከእኛ መካከል ተለይተው ወጥተዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ። |
በድንጋያማ ቦታ ላይ የወደቀውም ቃሉን ሲሰሙ በደስታ የሚቀበሉ ናቸው፤ እነዚህ ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር ስለሌላቸው በፈተና ጊዜ ፈጥነው የሚክዱ ናቸው።
ምናምንቴ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣
ይሁን እንጂ፣ “ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል” ደግሞም፣ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል።
ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። እንዲህ ያለ ማንኛውም ሰው አታላይና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።