1 ቆሮንቶስ 9:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ለእናንተ ግን በርግጥ ሐዋርያ ነኝ፤ ምክንያቱም በጌታ የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና፥ ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌታ የሐዋርያነቴ ማረጋገጫ ማኅተም እናንተ ስለ ሆናችሁ ለሌሎቹ እንኳ ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተ ግን በእርግጥ ሐዋርያ ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌሎች ሐዋርያቸው ባልሆንም ለእናንተስ ሐዋርያችሁ እኔ ነኝ፤ በጌታችን የሐዋርያነቴ ማኅተም እናንተ ናችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐዋርያነቴ ማኅተም በጌታ እናንተ ናችሁና ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን ለእናንተስ ምንም ቢሆን ሐዋርያ ነኝ። |
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በርሱ ላይ ዐትሟልና።”