1 ቆሮንቶስ 7:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሰው ተገርዞ ሳለ ቢጠራ፣ እንዳልተገረዘ ሰው አይሁን፤ ሳይገረዝም ተጠርቶ ከሆነ አይገረዝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደሆነ፥ መገረዝን አይፈልግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው ከተገረዘ በኋላ የተጠራ ከሆነ እንዳልተገረዘ ለመሆን አያስብ፤ ሳይገረዝ የተጠራ ከሆነም መገረዝን አይፈልግ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተገዝሮ ሳለ የተጠራ ቢኖር አለመገዘርን አይመኝ፤ ያልተገዘረም ቢጠራ ከዚያ ወዲያ አይገዘር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። |
በአሕዛብ መካከል የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉና ልጆቻቸውን እንዳይገርዙ፣ በቈየው ልማዳችን መሠረት እንዳይኖሩ እንደምታስተምር ስለ አንተ ተነግሯቸዋል።
በዚያ ግሪክ ወይም ይሁዲ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ አረማዊ ወይም እስኩቴስ፣ ባሪያ ወይም ጌታ ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።