እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
1 ቆሮንቶስ 5:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመካከላችሁ የዝሙት ርኩሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኩሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል፤ የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመካከላችሁ አሳፋሪ የዝሙት ሥራ መኖሩ ይወራል፤ እንዲህ ዐይነቱ የዝሙት ሥራ በአሕዛብ ዘንድ እንኳ የማይደረግ ነው፤ ይኸውም የእንጀራ እናቱን እንደ ሚስት አድርጎ የሚኖር አለ ተብሎአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና። |
እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋራ የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለ ወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ።
ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ ንጉሡም ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው የሄደውን ዐሥሩን ቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፣ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ።
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቷል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።
የአባታቸውን መኝታ የሚደፍሩ ሰዎች በውስጥሽ አሉ፤ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ ባልሆኑበት በወር አበባቸው ጊዜ ሴቶችን በማስገደድ የሚደፍሩ በመካከልሽ ይገኛሉ።
የችግረኞችን ራስ፣ በምድር ትቢያ ላይ ይረግጣሉ፤ ፍትሕንም ከጭቍኖች ይነጥቃሉ፤ አባትና ልጅ ከአንዲት ሴት ጋራ ይተኛሉ፤ እንዲህም እያደረጉ ቅዱስ ስሜን ያረክሳሉ።
ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ።
ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋራ እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋራ ምግብ እንኳ አትብሉ።
ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝሮች፣ ወንደቃዎች፣ ግብረ ሰዶማውያን፣
ዳግመኛም ስመጣ አምላኬ በእናንተ ፊት ያዋርደኝ ይሆን ብዬ እፈራለሁ፤ ይኸውም ብዙዎች ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኀጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፣ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን ነው።
እንግዲህ እኔ የጻፍሁላችሁ ስለ በደለው ወይም ስለ ተበደለው ሰው አይደለም፤ ነገር ግን ለእኛ ምን ያህል ታማኞች እንደ ሆናችሁ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን እንድታዩ በማለት ነው።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”