1 ቆሮንቶስ 4:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ “እኔን የምትመስሉ ሁኑ፤” ብዬ እለምናችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የእኔን ምሳሌነት እንድትከተሉ እለምናችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ! እኔን እንድትመስሉ እማልዳችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። |
ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማንኛውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋራ ይሆናል።