ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ዘወር ብሎ፣ “አንተ ሰይጣን፤ ወደ ኋላዬ ሂድ! የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በሐሳብህ ስለሌለ መሰናክል ሆነህብኛል” አለው።
1 ቆሮንቶስ 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ በክርስቶስ ገና ሕፃናት እንደ መሆናችሁ፣ እንደ ሥጋውያን እንጂ እንደ መንፈሳውያን ልናገራችሁ አልቻልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! እኔም፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወድሞች ሆይ፥ እኔስ የሥጋና የደም እንደ መሆናችሁ፥ ክርስቶስንም በማመን ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ እንደ መንፈሳውያን ላስተምራችሁ አልቻልሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። |
ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ዘወር ብሎ፣ “አንተ ሰይጣን፤ ወደ ኋላዬ ሂድ! የሰው እንጂ የእግዚአብሔር ነገር በሐሳብህ ስለሌለ መሰናክል ሆነህብኛል” አለው።
በበሰሉ ሰዎች መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፤ ይሁን እንጂ የዚህችን ዓለም ጥበብ ወይም የሚጠፉትን የዚህችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም።
ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።