ዘካርያስ 6:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፦ ‘ቅርንጫፉ በቦታው ስለሚስፋፋ ቅርንጫፍ የሚባል ስም ያለው ይህ ሰው ነው። ባለበት ስፍራ በቅሎ ገናና ይሆናል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ እንደገና ይሠራል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለርሱም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እነሆ፤ ስሙ ቅርንጫፍ የተባለው ሰው ይህ ነው፤ እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ ይሠራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቁጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የጌታንም መቅደስ ይሠራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቍጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የእግዚአብሔርንም መቅደስ ይሠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቍጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የእግዚአብሔርንም መቅደስ ይሠራል። |
ሠራተኞቹ የቤተ መቅደሱን መሠረት ማኖር በጀመሩበት ጊዜ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው በእጃቸው እምቢልታ በመያዝ የአሳፍ ቤተሰብ ተወላጆች የሆኑ ሌዋውያንም ጸናጽል ይዘው በረድፍ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከንጉሥ ዳዊት ዘመን ጀምሮ ተያይዞ በመጣው መመሪያ መሠረት በመዝሙር እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ስለዚህም በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተሠርቶ ወደነበረበት ስፍራ በደረሱበት በሁለተኛው ዓመት፥ በሁለተኛው ወር፥ ዘሩባቤል፥ ኢያሱና ሌሎቹም የሀገራቸው ልጆች፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ባጠቃላይም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው የመጡት ምርኮኞች ሥራውን ጀመሩ። ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ሌዋውያን ሁሉ የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ሥራ ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ።
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በምድሪቱ ያለውን የተክልና የዛፍ ቅርንጫፍ ልምላሜ የተዋበና የተከበረ ያደርገዋል፤ ከእስራኤል ወገን ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ምድሪቱ በምታስገኘው ሰብል ደስታና ኲራት ይሰማቸዋል።
አገልጋዬ በደረቅ ምድር ላይ እንደሚወጣ ሥርና እንደ ቡቃያ አድጓል፤ እንመለከተው ዘንድ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እርሱን እንወደው ዘንድ ከመልኩ አንዳች እንኳ የሚስብ ደም ግባት የለውም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዳዊት ዘር መካከል ጻድቅ የሆነውን ለንጉሥነት የምመርጥበት ጊዜ ይመጣል፤ ያም ንጉሥ በጥበብ ያስተዳድራል፤ በምድሪቱም ሁሉ ላይ ትክክልና ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል።
በዚያን ጊዜ የዳዊት ዘር ቅርንጫፍ የሆነ አንድ ጻድቅ ንጉሥ እመርጣለሁ፤ ያም ንጉሥ በአገሪቱ ላይ ቅን የሆነውን ነገር ያደርጋል፤ ትክክለኛ ፍርድም ይሰጣል።
ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁትና የቀድሞ አባቶቻቸውም በኖሩባት ምድር ይኖራሉ፤ በዚያችም ምድር እነርሱና ልጆቻቸው ዘሮቻቸውም ሳይቀሩ ለዘለዓለም ይኖራሉ፤ እንደ አገልጋዬ እንደ ዳዊት ያለ ንጉሥ በእነርሱ ላይ ለዘለዓለም ይነግሣል።
ቀጥሎም የቤተ መቅደሱ ማእከል ወደ ሆነው የተቀደሰ ስፍራ አስገባኝ፤ ወደ እርሱ የሚወስደውንም መተላለፊያ ሲለካ የሁለቱ ጐን ትይዩ ርዝመት ስድስት ክንድ ሆነ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ፈራርሶ እንደ ወደቀ ቤት የነበረውን የዳዊትን ሥርወ መንግሥት መልሼ የማቋቊምበት ጊዜ ይመጣል፤ ቅጽሩን እጠግናለሁ፤ ፍርስራሹንም አድሳለሁ፤ በቀድሞ ዘመን እንደ ነበረውም አድርጌ እሠራዋለሁ፤
እርሱም ሰላማቸው ይሆናል። አሦራውያን ምድራችንን ለመውረር ቢመጡና በምሽጎቻችን ላይ ቢወጡ ሰባት ጠባቂዎችንና ስምንት መሪዎችን በእነርሱ ላይ እናስነሣለን።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ።
ሊቀ ካህናት ኢያሱ ሆይ! ይህን ስማ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር በክህነት የምታገለግሉና ወደ ፊት ለሚሆነው መልካም ነገር ምልክት የምትሆኑ ይህን አድምጡ፤ ‘ቅርንጫፍ’ ተብሎ የሚጠራውን አገልጋዬን ወደ ፊት እልካለሁ።
“ለሠራዊት አምላክ ቤተ መቅደስን እንደገና ለመሥራት መሠረት በተጣለበት በቅርብ ጊዜ የነበሩ ነቢያት የተናገሩትን ቃል የሰማችሁ እናንተ አይዞአችሁ በርቱ!
እኔም እንዲህ እልሃለሁ፤ አንተ (ጴጥሮስ)፥ አለት ነህ፤ በዚህችም የመሠረት ድንጋይ ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ ይህችንም ቤተ ክርስቲያን የሞት ኀይል እንኳ አያሸንፋትም።
በአጠገቡ ያልፉ የነበሩትም ሰዎች ራሳቸውን በንቀት እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይሰድቡት ነበር፦ “አዬ፥ አንተ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራው!
በመስቀሉ ፊት ለፊት ቆሞ የነበረ የመቶ አለቃ ኢየሱስ እንዴት ነፍሱ ከሥጋው እንደ ተለየች ባየ ጊዜ፥ “ይህ ሰው በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፤” አለ።
ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፥ “ሙሴ በሕግ መጽሐፍ፥ ነቢያትም በትንቢት መጻሕፍት ስለ እርሱ የጻፉለትን አገኘነው፤ እርሱም የዮሴፍ ልጅ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነው” አለው።
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”