ቲቶ 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮችም ለጌቶቻቸው እንዲታዘዙ፥ በሁሉም ነገር እንዲያስደስቱአቸው፥ ክፉ ቃል እንዳይመልሱላቸው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮች ለጌቶቻቸው በማንኛውም ነገር እንዲገዙ፣ ደስ እንዲያሰኟቸውና የዐጸፋ ቃል እንዳይመልሱላቸው አስተምር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባርያዎች ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙና በነገር ሁሉ ደስ እንዲያሰኙአቸው ንገራቸው፤ እንዲሁም ሳይቃወሙና የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው። |