ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው።
ቲቶ 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወዱ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ማስተማር ይችላሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ወጣት ሴቶችን ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወድዱ ያስተምሩአቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቆነጃጅትም የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ፥ ባሎቻቸውን የሚወዱ፥ ልጆቻቸውን የሚወዱ፥ ራሳቸውን የሚገዙ፥ ንጹሖች፥ በቤት የሚሠሩ፥ በጎዎች፥ ለባሎቻቸው የሚታዘዙ እንዲሆኑ ይምከሩአቸው። |
ባሎቻቸው የሞቱባቸው በዕድሜ ያልገፉ ሴቶች ሥጋዊ ምኞታቸው አሸንፎአቸው ለክርስቶስ ያላቸው ፍቅር ሲቀነስ ባል ማግባት ስለሚፈልጉ እነርሱን በመበለቶች መዝገብ አትጻፋቸው።
ስለዚህ በዕድሜአቸው ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፥ ልጆችን እንዲወልዱ፥ ቤታቸውንም በሚገባ እንዲያስተዳድሩ እመክራለሁ፤ በዚህ ዐይነት ጠላት ለስም ማጥፋት ምክንያት ያጣል።
እንዲሁም በዕድሜ የገፉ ሴቶች በጠባያቸው የተከበሩ እንዲሆኑ እንጂ ሐሜተኞችና፥ የመጠጥ ሱሰኞች እንዳይሆኑና መልካሙን ትምህርት እንዲያስተምሩ ምከራቸው።