በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው።
ሮሜ 8:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን ለሚወዱና እንደ ፈቃዱም ለተጠሩት ሰዎች እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለበጎ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ ለሚወድዱትና እንደ ሐሳቡ ለተጠሩት፣ ነገር ሁሉ ተያይዞ ለበጎ እንዲሠራ እንደሚያደርግላቸው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የሚወዱትን ምርጦቹን በበጎ ምግባር ሁሉ እንደሚረዳቸው እናውቃለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። |
በእርግጥ እናንተ ክፉ ነገር መክራችሁብኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ወደ መልካም ነገር ለወጠው፤ ይህንንም ያደረገው አሁን በሕይወት ያሉትን የብዙ ሰዎችን ሕይወት ለማትረፍ ብሎ ነው።
“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።
ባቢሎንን ማንም የማይኖርባት ምድረ በዳ እንድትሆን ለማድረግ እግዚአብሔር ያቀደውን የሚፈጽምበት ጊዜ ከመሆኑ የተነሣ፥ ምድር በመናወጥ ትንቀጠቀጣለች።
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ።
ይሁን እንጂ መጽሐፍ፥ “የሰው ዐይን ያላየውን፥ የሰው ጆሮ ያልሰማውን፥ የሰው ልብ ያላሰበውን፥ እግዚአብሔር ለሚወዱት አዘጋጅቶአል” ይላል።
ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን።
ሽልማቴንም ለማግኘት በፊቴ ወዳለው ግብ እሮጣለሁ፤ ይህም ሽልማት እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ወደ ላይ ጠርቶ የሚሰጠኝ ሕይወት ነው።
እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን።
ነገር ግን “ጌታ የራሱ የሆኑትን ያውቃል፤” እንዲሁም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ጸንቶ ይኖራል።
እነዚያ የተጠሩት እግዚአብሔር በተስፋ የሰጠውን ዘለዓለማዊ ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን ማእከላዊ አስማሚ ሆኖአል፤ ይህም የሆነው ሰዎችን በመጀመሪያው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ከሠሩት ኃጢአት ለማዳን እርሱ በመሞቱ ነው።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።
ፍቅር ማለት እንዲህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን ስለ ወደድነው ሳይሆን እርሱ ስለ ወደደንና ኃጢአታችንን እንዲደመስስ ልጁን ስለ ላከልን ነው።