ሮሜ 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በሞተ ጊዜ ኃጢአት በእርሱ ላይ ሥልጣን እንዳይኖረው በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ ሞቶአል፤ አሁንም በሕይወት ሲኖር ለእግዚአብሔር ይኖራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቷል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሱ ሞቷልና፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኃጢአት ሞቷል፤ መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞቱም ኀጢአትን ሻራት፤ የተነሣም ለእግዚአብሔር ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል። |
ከሰው ባሕርይ ደካማነት የተነሣ ሕግ ሊያደርገው ያልቻለውን እግዚአብሔር አድርጎታል፤ የገዛ ልጁንም በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌነት በኃጢአት ምክንያት ልኮ በሥጋው ኃጢአትን በፍርድ አስወገደ።
በሕይወት ያሉት ሁሉ ለእነርሱ ለሞተውና ከሞትም ለተነሣው እንዲኖሩ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ለራሳቸው ሲሉ እንዳይኖሩ ክርስቶስ ለሁሉም ሞተ።
ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።
ለሙታን ሳይቀር ወንጌል የተሰበከውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ በመንፈሳቸው ግን እግዚአብሔር በሚኖረው ዐይነት በሕይወት ይኖራሉ።