ሮሜ 15:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜም የክርስቶስን በረከት በሙላት ይዤላችሁ እንደምመጣ ዐውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እናንተም ስመጣ፣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንደምመጣ ዐውቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እናንተም ስመጣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንደምመጣ አውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ ወንጌል በረከት ፍጹምነት እንደምትመጣ አምናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እናንተም ስመጣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንድመጣ አውቃለሁ። |
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
አሁን ግን በዚህ አካባቢ ባሉት አገሮች የምሠራባቸው ቦታዎች ስለሌሉ፥ እንዲሁም ከብዙ ዓመቶች ጀምሬም እናንተን ለመጐብኘት ከፍ ያለ ምኞት ስላለኝ
እኔ ከቅዱሳን ሁሉ የማንስ ብሆንም እንኳ ወሰን የሌለውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ እንዳበሥር በእግዚአብሔር ጸጋ ይህ ዕድል ተሰጠኝ።
እንዲሁም የእግዚአብሔርን ልጅ በማወቅ በእምነት ወደሚገኘው አንድነት ደርሰን፥ ክርስቶስ ፍጹምና ሙሉ እንደሆነው ዐይነት እኛም ሙሉ ሰው እንድንሆን ነው።