ሮሜ 15:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም የመቄዶንያና በአካይያ የሚገኙ የእግዚአብሔር ወገኖች በኢየሩሳሌም ላሉት ድኾች የገንዘብ ርዳታ ለመላክ በፈቃዳቸው ስለ ወሰኑ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም መቄዶንያና አካይያ፣ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል የሚገኙትን ድኾች ለመርዳት ተነሣሥተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ለመርዳት ወደዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ላሉ ድሆች አስተዋጽፅኦ ለማድረግ ተባብረዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መቄዶንያና አካይያ በኢየሩሳሌም ቅዱሳን መካከል ያሉትን ድሆች ይረዱ ዘንድ ወደዋልና። |
በጎቹን ይገዙና ይሸጡ ለነበሩት ሰዎች ተቀጥሬ እንዲታረዱ ለተፈረደባቸው የበጎች መንጋ እረኛ ሆንኩ፤ መንጋውንም በማሰማራበት ጊዜ ሁለት በትሮችን ወሰድኩ፤ አንደኛውን በትር “ተወዳጅ” ብዬ ጠራሁት፤ ሌላውን በትር “አንድነት” ብዬ ጠራሁት።
ንጉሡም ‘በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእነዚህ ከወንድሞቼ አነስተኛ ለሆነው ለአንዱ እንኳ ያደረጋችኹት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው!’ ሲል ይመልስላቸዋል።
ኢየሱስ ቀና ብሎ ወደ ደቀ መዛሙርቱ እየተመለከተ እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ናትና፥ እናንተ ድኾች የተባረካችሁ ናችሁ!
ከዚያም ተነሥተን ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ ፊልጵስዩስ በመቄዶንያ የምትገኝ ታላቅ ከተማና የሮማውያን ቅኝ አገር ነበረች፤ በዚህችም ከተማ ጥቂት ቀኖች አሳለፍን።
ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈሱ አስቦ “እዚያ ከደረስኩ በኋላ ወደ ሮም መሄድ አለብኝ” አለ።
ወንድሞች ሆይ! የእስጢፋኖስ ቤተሰብ በአካይያ አገር የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ምእመናንን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ።
ልጐበኛችሁ ያቀድኩትም ወደ መቄዶንያ ሳልፍና ከዚያም በምመለስበት ጊዜ ነበር፤ በዚህም ሁኔታ ወደ ይሁዳ ምድር በማደርገው ጒዞዬ ትረዱኛላችሁ ብዬ አስቤ ነበር።
ከእናንተ ጋር ሳለሁ ችግር በደረሰብኝ ጊዜ ከመቄዶንያ የመጡ ወንድሞች በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ይረዱኝ ስለ ነበር በማንም ሸክም አልሆንኩም፤ እስከ አሁን በእናንተ ላይ በምንም ነገር ሸክም አልሆንኩም፤ ለወደፊትም ሸክም አልሆንባችሁም።
ይህ የምትፈጽሙት የልግሥና አገልግሎት የክርስቲያኖችን ችግር ከማስወገዱም በላይ ሰዎች ለእግዚአብሔር ብዙ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደርጋቸዋል።
“የዐካይያ ሰዎች ከዐለፈው ዓመት ጀምረው ለመርዳት ዝግጁዎች ናቸው” ብዬ በመቄዶንያ ሰዎች ዘንድ ስለ እናንተ የምመካው ትጋታችሁን ስለማውቅ ነው፤ የእናንተም ትጋት ሌሎችን አነሣሥቶአል።
የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ወደ እናንተ መጥተው ያልተዘጋጃችሁ ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን፤ እናንተማ በጣም ታፍራላችሁ።
ከዚህም በቀር ወንጌልን ለማብሠር በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በፊልጵስዩስ ከምትገኙት አማኞች በቀር በመስጠትም ሆነ በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ማኅበረ ምእመናን እንዳልነበረ እናንተው ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
የጌታ ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ያላችሁ እምነት በሁሉ ቦታ ታውቆ ነበር፤ በዚህ ምክንያት እኛ ስለዚህ ጉዳይ ምንም መናገር አያስፈልገንም።
ወደ መቄዶንያ ስሄድ ሳለሁ ዐደራ እንዳልኩህ እዚያ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የሐሰት ትምህርት እንዳያስተምሩ ታደርጋቸው ዘንድ በኤፌሶን ተቀመጥ።