ሮሜ 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ወንድምህን ላለማሰናከል ሥጋን አለመብላት፥ የወይን ጠጅን አለመጠጣት፥ ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ መልካም ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለወንድምህ መሰናከል ምክንያት የሚሆነውን ሥጋን አለመብላት፣ ወይንን አለመጠጣት፣ ወይም አንዳች ነገርን አለማድረግ መልካም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወይም ማንኛውም ወንድምህ የሚሰናከልበትን ነገር አለማድረግ መልካም ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወንድም ዕንቅፋት ከመሆን ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋን አለመብላት ወይንንም አለመጠጣት ወንድምህም የሚሰናከልበትን አለማድረግ መልካም ነው። |
ነገር ግን ለጊዜው ነው እንጂ በልቡ ውስጥ ሥር አልሰደደም፤ ስለዚህ በቃሉ ምክንያት አንዳች ችግር ወይም ስደት በደረሰበት ጊዜ ቶሎ ይሰናከላል።
ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፦ “አንተ ሰይጣን! ከኋላዬ ሂድ! አንተ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር ስለማታስብ ለእኔ እንቅፋት ነህ” አለው።
ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።