ሮሜ 14:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምግብም ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አናፍርስ። ምግብ ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ሌላውን ሰው የሚያሰናክል ምግብ መብላት ስሕተት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምግብ ስትል የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ለሌላው ሰው የመሰናከያ ምክንያት የሚሆነውን መብላት ስሕተት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ነገር በራሱ ንጹሕ ነው፤ በመጠራጠር የተበላ እንደሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፍጥረት አናፍርስ፤ ለንጹሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰውስ ክፉው ነገር በመጠራጠር መብላት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፥ በመጠራጠር የተበላ እንደ ሆነ ግን ለዚያ ሰው ክፉ ነው። |
“ማንም ሰው በእኔ ከሚያምኑት ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከሚያስት ከባድ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢጣልና ቢሰጥም ይሻለዋል።”
ስለዚህ ወንድምህን ላለማሰናከል ሥጋን አለመብላት፥ የወይን ጠጅን አለመጠጣት፥ ወይም ማንኛውንም የሚያሰናክል ነገር አለማድረግ መልካም ነው።
እኛ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጃቸውን መልካም ሥራዎች እንድንሠራ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እንደገና የተፈጠርን የእግዚአብሔር ፍጡሮች ነን።
ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ሕይወት ውስጥ የጀመረ አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በሚመለስበት ቀን ወደ ፍጻሜ እንደሚያደርሰው እርግጠኛ ነኝ።
ለንጹሖች፥ ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሶችና ለማያምኑ ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው የረከሰ ነው።