ሮሜ 12:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ክፉውን ነገር በመልካም ነገር አሸንፍ እንጂ በክፉ ነገር አትሸነፍ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉውን በመልካም ሥራ ድል ንሣው እንጂ ክፉውን በክፉ ድል አትንሣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ። |
ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት።