ዮሴፍ አገልጋዮቹን “ለእነዚህ ሰዎች በየስልቻዎቻቸው እህል ሙሉላቸው፤ ገንዘባቸውንም መልሳችሁ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ቋጥሩላቸው፤ ለጒዞአቸውም ስንቅ አስይዙአቸው” ብሎ አዘዘ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
ሮሜ 12:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከመበቀል ይልቅ ጠላትህን ቢርበው አብላው፤ ቢጠማውም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ በዕፍረት እሳት ታቃጥለዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይልቁንስ፣ “ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው። ይህን በማድረግህም የእሳት ፍም በራሱ ላይ ትከምራለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጠላትህ ቢርበው አብላው፤ ቢጠማው አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላትህ ቢራብ አብላው፤ ቢጠማም አጠጣው፤ ይህን ብታደርግ የእሳት ፍሕም በራሱ ላይ ትከምራለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። |
ዮሴፍ አገልጋዮቹን “ለእነዚህ ሰዎች በየስልቻዎቻቸው እህል ሙሉላቸው፤ ገንዘባቸውንም መልሳችሁ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ቋጥሩላቸው፤ ለጒዞአቸውም ስንቅ አስይዙአቸው” ብሎ አዘዘ። ይህም ከተደረገላቸው በኋላ፥
ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው።
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።