ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።
ራእይ 19:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የነገሥታትን ሥጋ፥ የጦር አዛዦችን ሥጋ፥ የብርቱ ጦረኞችን ሥጋ፥ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ፥ የጌቶችንና የአገልጋዮችን ሥጋ፥ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፥ የማንኛውንም ሰው ሁሉ ሥጋ ኑ ብሉ!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትሰበሰቡትም የነገሥታትን ሥጋ፣ የጦር አዛዦችን ሥጋ፣ የብርቱ ሰዎችን ሥጋ፣ የፈረሶችንና የፈረሰኞችን ሥጋ እንዲሁም የሰዎችን ሁሉ፣ ይኸውም የጌቶችንና የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ እንድትበሉ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባርያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ ትበሉ ዘንድ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። |
ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል።
የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያቀዱት ነገር ሁሉ በዚህ ስፍራ እንዳይፈጸም አደርጋለሁ፤ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና በጦርነትም እንዲገድሉአቸው አደርጋለሁ፤ ሬሳቸውንም የሰማይ ወፎችና የምድር አራዊት እንዲበሉት አደርጋለሁ።
አንተንና የወንዞችህን ዓሣዎች ሁሉ ወደ በረሓ እወረውራችኋለሁ፤ ሬሳህም ተነሥቶ ሳይቀበር በመሬት ላይ ወድቆ ይቀራል፤ ለወፎችና ለአራዊትም ምግብ እንዲሆን አደርገዋለሁ።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንተም የሰው ልጅ ሆይ! ለተለያዩ የአሞራ ዘሮችና ለአራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ‘በእስራኤል ተራራዎች ላይ በማዘጋጅላችሁ ታላቅ የመሥዋዕት በዓል ሥጋን ለመብላትና ደምን ለመጠጣት ከየአቅጣጫው ተሰብስባችሁ ኑ።’
ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ነው የሚወሰዱት” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም “በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበሰባሉ” ሲል መለሰላቸው።
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
ሁለተኛው አውሬ ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፥ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች፥ ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች፥ ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግንባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥር ቀንዶች አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ወደ ጥፋት ያደርሱአታል፤ ራቁትዋን ያስቀሩአታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤
በዚህች ቀን እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ያጐናጽፈኛል፤ እኔም ራስህን እቈርጣለሁ፤ የፍልስጥኤማውያንንም ወታደሮች ሥጋ ለአሞራዎችና ለአራዊት ምግብ አድርጌ እሰጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ መላው ዓለም በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ያውቃል።