ራእይ 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያን ያኽል ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፋ!” ይላሉ። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፥ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፥ በመርከብ ላይ የሚሠሩ ሁሉ፥ በባሕር ላይ የሚነግዱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሯቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን የሚያህል ታላቅ ሀብት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና፤” የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፤ |
እነዚህ ሁለቱም ነገሮች በቅጽበት በአንድ ቀን በአንቺ ላይ ይደርሳሉ፤ ምንም ያኽል መተትሽ ትልቅ፥ ጥንቈላሽም ብዙ ቢሆን የልጆችና የባል ሞት በአንቺ ላይ በሙላት ይደርሳል።
የመርከብ አዛዡም ወደ እርሱ ቀርቦ “እንዴት ትተኛለህ? ኧረ እባክህ ተነሥና ወደ አምላክህ ጸልይ፤ ምናልባት ራርቶልን ሕይወታችንን ያድን ይሆናል” አለው።
“ያየሃቸው ዐሥሩ ቀንዶች ገና ያልነገሡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ለአንዲት ሰዓት ከአውሬው ጋር እንዲነግሡ የመንገሥ ሥልጣን ያገኛሉ።
አውሬውና ያየሃቸው ዐሥር ቀንዶች አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ወደ ጥፋት ያደርሱአታል፤ ራቁትዋን ያስቀሩአታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሏታል፤
በራሳቸው ላይ አቧራ ነሰነሱ፤ እያለቀሱና እያዘኑም እንዲህ እያሉ ይጮኻሉ፤ “በባሕር ላይ መርከቦች ያላቸው ሁሉ በእርስዋ ሀብት ሀብታሞች የሆኑ፥ ያቺ ታላቅ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስለ ወደመች ወዮላት! ወዮላት!”