ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤ ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም።
ምሕረቴን ግን ከርሱ አላርቅም፤ ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
ኃጢአታቸውን በበትር፥ በደላቸውንም በመቅሠፍት እጐበኛታለሁ።
ለስሜ መጠሪያ ቤት የሚሠራልኝም እርሱ ነው፤ የመንግሥቱንም ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ።
እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤ ስሕተት በሚፈጽምበትም ጊዜ አባት ልጁን እንደሚቀጣ እቀጣዋለሁ፤
ይሁን እንጂ በእርሱ ቦታ አንተ ትነግሥ ዘንድ ባስወገድኩት በሳኦል ላይ እንዳደረግሁ ዘለዓለማዊ ፍቅሬን ከልጅህ አላርቅም።
ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”
ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።
ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ
ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤ ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።
እግዚአብሔር ጠላቶቹን ሁሉ በሥልጣኑ ሥር እስኪያደርግለት ድረስ ክርስቶስ መንገሥ ይገባዋል።
በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔር የማይለወጡትንና የማይዋሽባቸውን ሁለቱን ነገሮች፥ ማለትም ተስፋውንና መሐላውን ሰጥቶናል፤ በእነዚህም በሁለቱ ነገሮች አማካይነት በፊታችን ያለውን ተስፋ አጥብቀን መያዝ እንድንችል መጠጊያ ለማግኘት ወደ እርሱ የሸሸን እኛ ታላቅ መጽናናትን እናገኛለን።
የእስራኤል ክብር የሆነ እግዚአብሔር አያብልም፤ ሐሳቡንም አይለውጥም፤ እርሱ እንደ ሰው ስላልሆነ ሐሳቡን አይለውጥም።”