መዝሙር 105:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በአገሩ ላይ ጨለማ እንዲሆን አደረገ፤ ይሁን እንጂ ግብጻውያን ትእዛዞቹን አልፈጸሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጨለማን ልኮ ምድሪቱን ጽልመት አለበሰ፤ እነርሱም በቃሉ ላይ ማመፅን ተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጨለማን ላከ፥ ጨለመባቸውም፥ በቃሉም ዐመፁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብዔል ፌጎርም ዐለቁ፥ የሞተ መሥዋዕትንም በሉ፤ |
ያ ቀን የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ የጧት ፀሐይ ወገግታ በተራሮች ላይ እንደሚያንሰራፋ፥ ታላቅና ኀያል የአንበጣ መንጋ በየቦታው ይንሰራፋል። ይህን የሚመስል ነገር ከዚህ በፊት አልታየም፤ ከእንግዲህ ወዲህም ምን ጊዜም ቢሆን አይታይም።
መላእክትን እንኳ ኃጢአት በሠሩ ጊዜ እግዚአብሔር ሳይራራላቸው በጨለመ ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ሆነው የፍርድን ቀን እንዲጠባበቁ ወደ ገሃነም ጣላቸው፤
እግዚአብሔርን ብትፈሩና ብታመልኩት፥ ቃሉንም ብታዳምጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ብትጠብቁ፥ እናንተና በእናንተ ላይ የነገሠው ንጉሥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትከተሉ ሁሉ ነገር ይሠምርላችኋል፤