ምሳሌ 31:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆችዋ አድናቆታቸውን ይገልጡላታል፤ ባልዋም ያመሰግናታል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቿ ተነሥተው ቡርክት ይሏታል፤ ባሏም እንዲሁ፣ ሲያመሰግናትም እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆችዋ ይነሣሉ፥ ምስጉን ነሽ ይሏታል፥ ባሏ ደግሞ እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፦ |
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
ሞገስ ያላት ሴት ትከበራለች፤ መልካም ጠባይ የሌላት ሴት ግን ውርደት ያገኛታል። ሰነፍ ሰው ሀብት ማግኘት አይችልም፤ ታታሪ ሰው ግን ሀብታም ይሆናል።
በአንተ ያለውን እውነተኛ እምነት አስታውሳለሁ፤ እንዲህ ዐይነቱ እምነት በመጀመሪያ በአያትህ በሎይድና በእናትህ በኤውኒቄ የነበረ ነው፤ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ።