ምሳሌ 31:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተሰብዋ ምግብ ለማዘጋጀትና ለሠራተኞችዋ ሥራ ለማከፋፈል ገና ሳይነጋ ትነሣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገና ሳይነጋ ትነሣለች ለቤትዋም ሰዎች ምግባቸውን፥ ለአገልጋዮችዋም ሥራ ትሰጣለች። |
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ታዲያ ቤተሰቦቹን በደንብ እንዲያስተዳድርለትና ለአገልጋዮቹም ምግባቸውን በተመደበው ጊዜ እንዲሰጣቸው ጌታው የሚሾመው ታማኝና ብልኅ መጋቢ ማን ነው?
በማግስቱ ኢያሱና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ማልደው ተነሡ፤ የሺጢምን ሰፈር ለቀው ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄዱ፤ ከመሻገራቸውም በፊት በዚያ ሰፈሩ፤