ልጆችን መገሠጽና መቅጣት ጥበብ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ልጅ ስድ ዐደግ የሆነ እንደ ሆነ ግን እናቱን ያሳፍራል።
የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
በትርና ተግሣጽ ጥበብን ይሰጣሉ፥ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።
እነዚህ የሰሎሞን ምሳሌዎች ናቸው፤ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሐዘንን ያተርፋል።
ብልኅ ሰው መከሩን በወቅቱ ይሰበስባል፤ በመከር ወራት የሚተኛ ግን ውርደት ይደርስበታል።
ልጁን የማይቀጣ አይወደውም ማለት ነው፤ ልጁን የሚወድ ግን ቀጥቶ ያሳድገዋል።
የሰነፍ ልጅ አባት ከሐዘንና ከብስጭት በቀር ምንም ደስታ የለውም።
ሰነፍ ልጅ አባቱን በሐዘን ላይ ይጥላል፤ በእናቱም ላይ መራራ ጸጸት ያመጣል።
የመመለስ ተስፋ ሳላቸው ልጆችህን በልጅነታቸው ቅጣቸው፤ ባትቀጣቸው ግን ለጥፋት አሳልፈህ እንደ ሰጠሃቸው ይቈጠራል።
በልጅ ልብ ውስጥ ሞኝነት አለ፤ የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያስወግደዋል።
ልጅን እንዴት መኖር እንደሚገባው ብታስተምረው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
ልጅህን ቅጣ፤ ዕረፍትና ሰላም በማግኘት ደስ ትሰኛለህ።
አንድ ባሪያ ከልጅነቱ ጀምሮ ተቀማጥሎ ካደገ መጨረሻው አያምርም።