ምሳሌ 25:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትዕግሥት ማግባባት ታላቅ ተቃውሞን ያበርዳል፤ መሪዎችን ሳይቀር በሐሳብ እንዲስማሙ ያደርጋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በትዕግሥት ገዥን ማግባባት ይቻላል፤ ለስላሳ አንደበትም ዐጥንት ይሰብራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ ገር ምላስ አጥንትን ይሰብራል። |
ከማሩም ጥቂት በእጁ ቈርጦ እየበላ መንገዱን ቀጠለ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ ቀርቦ ከያዘው ማር. ሰጥቶአቸው በሉ፤ ነገር ግን ሶምሶን ያንን ማር. ያገኘው ከሞተው አንበሳ በድን ውስጥ መሆኑን አልነገራቸውም።
ከናባል አገልጋዮች አንዱም የናባልን ሚስት አቢጌልን እንዲህ አላት፤ “ዳዊት ካለበት በረሓ መልእክተኞችን ከሰላምታ ጋር ወደ ጌታችን ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን በስድብ አዋረዳቸው፤